COVID-19: አማርኛ

ተጋላጭነት ያለው ህዝብ

ከ COVID-19 (ኮቪድ-19 ኮሮና ቫይረስ) በበሽታው ለመያዝ በከፍተኛ ስጋት ውስጥ ከሆኑ፦

  • አቅርቦቶችን ያከማቹ
  • በየእለቱ በእርስዎና በሌሎች መካከል ያለውን ርቀት ለመጠበቅ ጥንቃቄ ያድርጉ
  • ህዝብ ወዳለበት ሲወጡ ከሌሎችና ከታመሙት ራቅ ይበሉ፣ ከንክኪ ይታቀቡ ፣ ሁልጊዜ እጆችዎን ይታጠቡ
  • በተቻለ መጠን ከማህበራዊ ስብሰባ ይታቀቡ::
  • ከመርከብና አላስፈላጊ ከሆኑ የአየር ጉዞ ይታቀቡ
  • በአካባቢዎ ነዋሪዎች ዘንድ የ COVID-19 (ኮቪድ-19 ኮሮና ቫይረስ) ወረርሽኝ ባለበት ጊዜ ለመጋለጥ ያለዎን እድል ለመቀነስ በተቻለ መጠን ከቤትዎ አይውጡ

ተጋላጭ የሆኑት ህዝቦችን የሚያካትተው የህብረተሰብ ክፍል፦

  • ከ 60 አመትና ከዚያ በላይ
  • የተለያየ በሽታ እንደ የልብ ህመም፣ የሳምባ በሽታ፣ የስኳር በሽታ፣ የኩላሊት በሽታ እና የተዳከመ የበሽታ መከላከያ ሲስተም ያላቸውን

ተጨማሪ ምክሮች

የተዘጋጁ አቅርቦቶች በእጅዎ ይኑርዎ

  • በማህበረሰብዎ ውስጥ የ COVID-19 (ኮቪድ-19 ኮሮና ቫይረስ) ወረርሽኝ ቢከሰት እና ምናልባት በቤትዎ ለተራዘመ ጊዜ መቆየት ካለብዎ የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎን አስፈላጊ የሆኑ ተጨማሪ መድሃኒቶችን የሚያገኙበትን መንገድ ይጠይቁ ፡፡
  • ተጨማሪ መድሃኒቶችን ማግኘት የማይችሉ ከሆነ የፖስታ ማዘዣ አገልግሎትን መጠቀምን አስቡ
  • ከፋርማሲ መደርደሪያ ላይ ሊያግኟቸው የሚችሉ ተጨማሪ መድሃኒቶችና የህክምና አቅርቦቶች (ቲሹ ወዘተ) ትኩሳትንና ሌሎች ምልክቶችን ለመቆጣጠር መድሃኒቶቹ በእጅዎ እንዳሉ እርግጠኛ ይሁኑ፤ ብዙ ሰዎች ከኮቪድ-19 በቤታቸው ይድናሉ።
  • እንዲዘጋጁና ለተወሰነ ጊዜ በቤትዎ እንዲቆዩ እንዲያስችልዎ በቂ የቤት ቁሳቁሶችና ግሮሰሪዎች በእጅዎ ይኑርዎ

በየቀኑ ጥንቃቄ ይውሰዱ

  • ከታመሙ ሰዎች ጋር ንክኪ እንዳያደርጉ ይጠንቀቁ
  • በየቀኑ ጥንቃቄ ይውሰዱ
    • ሁልጊዜ እጅዎትን ይታጠቡ
    • እጅዎትን በውሃና በሳሙና ቢያንስ ለ20 ሰከንዶች ይታጠቡ በተለይም ከተናፈጡ ፣ ካሳሉ ወይም ካስነጠሱ በኋላ ወይም ሰው የበዛበት ስፍራ ከነበሩ። ውሃና ሳሙና ከሌለ ቢያንስ 60 ከመቶ አልኮል በሆነ የእጅ ማጽጃ ይጠቀሙ
    • በተቻለ መጠን በህዝብ ስፍራ በተደጋጋሚ ሊነኩ ከሚችሉ ነገሮች ይታቀቡ። የኤሊቬተር ቁልፎች፣ የመዝጊያ እጀታዎች፣ የደረጃ ድጋፎች፣ ከሰዎች ጋር መጨባበጥ ወዘተ አንድነገር የግድ መንካት ካለብዎ እጅዎን ወይም ጣትዎን ለመሸፈን ቲሹ ወይም ኮሌታዎን ይጠቀሙ።
    • በህዝባዊ ስፍራ ያሉ ነገሮችን ከነኩ በኋላ እጆችዎን ይታጠቡ
    • ፊትዎን፣አፍንጫዎን፣ ዓይንዎን ወዘተ ክመንካት ይቆጠቡ።
    • ከቤትዎ ጀርም ለማስወገድ ጽዳትና የጽዳት ኬሚካል ይጠቀሙ በተደጋጋሚ የሚነኩ ቦታዎች ላይ መደበኛ ጽዳት ያድርጉ( ለምሳሌ ጠረጴዛዎች፣በር መክፈቻዎች፣ መብራት ማብርያ ማጥፊያዎች፣ እጀታዎች፣ ዴስኮች፣ ሽንትቤቶች ፣ መታጠቢያ ገንዳዎች እና ሴልፎኖች)
    • ከህዝብ በተለይም የ'አየር እጥረት ካለበት ቦታ ይራቁ፡ እንደ ኮቪድ-19 መተንፈሻን ሊያጠቁ በሚችሉ ቫይረሶች ሰው ችምችም ብሎ በሚገኝበትና በቂ የአየር ዝውውር በሌለበት ከህዝቡ መሃል የታመሙ ቢኖሩ ለመጋለጥ ያለዎት እድል ይጨምራል።
    • የአውሮፕላን ጉዞዎችን ጨምሮ ሁሉንም አላስፈላጊ የሆኑ ጉዞዎችን ያስወግዱ ፣ በተለይም ክሩስ መርከቦችን።
    • በህብረተሰብዎ መካከል የ COVID-19 (ኮቪድ-19 ኮሮና ቫይረስ) ወረርሽኝ ካለ በእርስዎና በሌሎች ስዎች መካከል ያለውን ርቀት ለመጠበቅ እንዲሁም በዚህ አዲስ በሽታ የመጋለጥን ስጋት ለመቀነስ ተጨማሪ እርምጃ ይውሰዱ።
    • በተቻለ መጠን በቤትዎ ይቆዩ
    • ምግብ ወደቤትዎ በቤተስብ ፣በህብረት ወይም በንግድ አውታሮች ሊመጣልዎ የሚችልበትን መንገድ ያጥኑ

ምናልባት ቢታመሙ እቅድ ይኑርዎ

ምልክቶችን እና የድንገተኛ ማስጠንቀቂያ ምልክቶችን ይመልከቱ

  • ምልክቶችን እና የድንገተኛ ማስጠንቀቂያ ምልክቶችን ይመልከቱ ትኩሳት ፣ ሳል ፣ የትንፋሽ እጥረት ጨምሮ ላሉት የ COVID-19 (ኮቪድ-19 ኮሮና ቫይረስ) ምልክቶች ትኩረት ይስጡ ፡፡ የበሽታ ምልክቶች እየባሰ እንደሆነ ከተሰማዎት ሐኪምዎጋ ይደውሉ።
  • ለ COVID-19 (ኮቪድ-19 ኮሮና ቫይረስ) የአደጋ ጊዜ ማስጠንቀቂያ ምልክቶችን ካጋጠምዎ ወዲያውኑ የሕክምና እርዳታ ያግኙ ፡፡ በአዋቂዎች ውስጥ የአደጋ ጊዜ ማስጠንቀቂያ ምልክቶች *:
  • የመተንፈስ ችግር ወይም የትንፋሽ እጥረት
  • በደረት ውስጥ የማያቋርጥ ህመም ወይም ግፊት
  • አዲስ ግራ መጋባት ወይም መቀስቀስ አለመቻል
  • ሰማያዊማ ከንፈር ወይም ፊት

* ይህ ዝርዝር ሁሉንም አካታች አይደለም ፡፡ ከባድ ወይም አሳሳቢ የሆኑ ሌሎች ምልክቶችን ለማግኘት እባክዎ የጤና ባለሙያዎን ያማክሩ።

ከታመሙ ምን ማድረግ እንዳለብዎ?

  • ቤት ይቆዩ እና ለሐኪምዎ ይደውሉ
  • ለጤና እንክብካቤ አቅራቢዎ ይደውሉ እና ስለ ህመምዎ ያሳውቋቸው ፡፡ ኮቪድ-19 እንዳለዎት ወይም ሊኖርዎት  እንደሚችል  ይንገሯቸው። ይህ እርስዎን እንዲንከባከቡ እና ሌሎች ሰዎች በበሽታው እንዳይጠቁ ወይም እንዳይጋለጡ ያግዳቸዋል ፡፡
  • በሆስፒታል ለማስተኛት በሚያደርስ ህመም ካልታመሙ በቤትዎ ማገገም ይችላሉ ፡፡
  • በቤት ውስጥ እራስዎን ለመንከባከብ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል (ሲዲሲ) መመሪያዎችን ይከተሉ፡፡
  • የድንገተኛ ጊዜ እርዳታ መቼ እንደሚያገኙ ይወቁ
  • ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን ማንኛውንም የድንገተኛ አደጋ ምልክቶች ካዩ ወዲያውኑ የሕክምና እርዳታ ያግኙ

ጠና ያሉ አዋቂዎችን ለመደገፍ ሌሎች ምን ማድረግ እንደሚችሉ?

ጠና ላሉ አዋቂዎች የማህበረሰብ ድጋፍ

  • ለ COVID-19 (ኮቪድ-19 ኮሮና ቫይረስ) ህብረተሰብን የማዘጋጀት ዕቅድ ጠና ያሉ አዋቂዎችንና አካለ ስንኩላንን ሊያካትት ይገባል በማህበረስባቸው የሚደግፋቸው ድርጅት የሚያስፈልጋቸው ሁሉ መሟላቱን ያረጋግጣል።
    • እነዚህ ግለሰቦች በማህበረሰቡ ውስጥ ይኖራሉ ብዙዎቹምጤንነታቸውን እና ነጻነታችውን ለመጠበቅ በቤታችው ወይም ደግሞ በማህበረሰቡ ውስጥ በሚደረግላቸው አገልግሎትና እርዳታ ይደገፋሉ ።
  • የረጅም ጊዜ እንክብካቤ መስጫ ተቋማት የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል ንቁ መሆን አለባቸው ፡፡ የረጅም ጊዜ እንክብካቤ ተቋማት መረጃ እዚህ ይገኛል

ቤተሰብና የተንከባካቢ እርዳታ

  • ወዳጅዎ ምን ዓይነት መድሃኒት እንደሚወስድ ይወቁ እና በእጃቸው ተጨማሪ እንዲኖራቸው ሊያግዟቸው እንደሚችሉ ይመልከቱ ፡፡
  • ምግብን እና ሌሎች የህክምና አቅርቦቶችን (ኦክስጅንን ፣ መቆጣጠር አለመቻል ፣ የኩላሊት እም ማጥሪያ ፣ ቁስልን መንከባከቢያ) የሚያስፈልግ እንደሆነ በመቆጣጠር የመጠባበቂያ ዕቅድ ይፍጠሩ ፡፡
  • ወደ መደብሮች የሚጓዙትን ጉዞዎች ለመቀነስ በቤትዎ ውስጥ ሊበላሹ የማይችሉ የምግብ ዓይነቶችን ያከማቹ፡፡
  • በእንክብካቤ መስጫ ተቋም ውስጥ የሚኖር ወዳጅዎን የሚንከባከቡ ከሆነ ሁኔታውን ይቆጣጠሩ ፣ ስለሌሎች ነዋሪዎች ጤና ደጋግመው ይጠይቁ እና ወረርሽኝ ካለ ፕሮቶኮሉን ይወቁ ፡፡

በተደጋጋሚ ስለ ኮቭድ-19 (ኮሮና ቫይረስ)  የሚነሱ ጥያቄዎች

COVID-19 (ኮቪድ-19 ኮሮና ቫይረስ)  ምንድን ነው?

COVID-19 (ኮቪድ-19 ኮሮና ቫይረስ) በሽታ (ኮቪድ19) በአዲስ ቫይረስ ምክንያት የሚከሰት የመተንፈሻ አካል ህመም   ነው። ከሰው ወደ ሰው ሊተላለፍ ይችላል። ይህ ቫይረስ ለመጀመሪያ ጊዜ በዉሀን፣ ቻይና ውስጥ ተለይቶ የታወቀ ሲሆን አሜሪካንም ጨምሮ ወደተለያዩ አገራት ተሰራጭቷል።

 በሽታው ከዚህ በፊት በሰዎች ላይ የተከሰተ ባለመሆኑ አዲስ ቫይረስ ነው፤፤ COVID-19 (ኮቪድ-19 ኮሮና ቫይረስ) በዓለም ዙሪያ፣  በሺዎች ላይ  የኢንፌክሽን ሕመም እና አንዳንዴም ሞትን አስከትሏል፤፤ ቫይረሱ ያለማቓረጥ  እየተስፋፋ ሲሆን አሜሪካን ጨምሮ ቢያንስ በ100 አገሮች፣ ዙሪያ የተሰራጨ መሆኑን ሪፖርት ተደርጏል። የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) በመጋቢት ወር የመጀመሪያዎቹ ቀናት  ውስጥ ስለ ኮቪድ-19 ወረርሽኙ መከሰት አውጇል።  

በአሁኑ ወቅት ለአደጋ የተጋለጡት እነማን ናቸው?  `

ማንኛም ሰው በኮቪድ-19 ሊታመም ይችላል። በሞንትጎመሪ ካውንቲ ካውንቲ በቾቪድ-19 የተጠቁት ብዙዎቹ መለስተኛና ልከኛ ምልክት ነው ያሳዩት።  

በአሁኑ ወቅት የከፋ ህመም ተጋላጭነት ስጋት ያለባቸው ሰዎች የሚጨምረዉ፡ 

  • አረጋውያን (ዕድሜያቸው 60 እና ከዛ በላይ የሆኑቱ ናቸው)
  • ከባድ ሥር የሰደደ የጤና ችግር ያላቸው ሰዎች እንደ፥:   የልብ ህመም ፣ የስኳር በሽታና፣ የሳንባ በሽታ ያለባቸው

የከፋ ህመም ተጋላጭነት ስጋት ላለበቸው ሰዎችና ከ60 ዓመት በላይ ለሆኑ ምን የጤና ምክረ ሀሳቦች አሉ?

ለኮሮናቫይረስ COVID-19 (ኮቪድ-19 ኮሮና ቫይረስ) በከፍተኛ ተጋላጭነት ስጋት ያለብዎት ከሆኑ ማድረግ ያለብዎት:-

  • የእራስዎን እና የሌሎችን ደህንነት ለመጠበቅ ዕለት ተዕለት በቂ  የማህበራዊ ግንኙት ርቀትን ይጠብቁ
  • አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር ቤት ይቆዩ፥ የቅርብ ለቅርብ ግንኙነትን ለገደብ ለሰዎች ብዙ የቦታ ክፍተት ይስጡ እጅዎን በየጊዜዉ ይታጠቡ፥፥
  • በተቻለ መጠን የማህበረሰብ ስብስብ እና ዝግጅቶችን አይሳተፉ፥፥.
  • ከማናቸውም የሽርሽርና የመዝናኛ የጉዞ ልማዶችንና አስፈላጊ ካልሆኑ የአየር ጉዞ ይታቀቡ።
  •  በኮቪድ-19 በሚተላለፍ ወረርሽኝ ጊዜ የመጋለጥ እድልን በበለጠ ለመቀነስ በቤትዎ ውስጥ ይቆዩ ፡፡
  • በማህበረሰብዎ አካባቢ COVID-19 (ኮቪድ-19 ኮሮና ቫይረስ) ወረርሽኝ ወቅት ቤትዎ ይቀመጡ ና ከሌሎች ሰዎች ጋር የቅርብ ግንኙነትዎን አቁሙ።

የከፋ ለህመም ተጋላጭነት ስጋት ያለባቸው ሰዎች የሚጨምረዉ፥

  •  እድሜያቸው 60 ና  ከዚያ በላይ የሆኑ አረጋውያን
  • አንዳንድ የጤና ቀውስ ያለባቸው ሰዎች እንደ የልብ ህመም ፥ የስኳር በሽታና፥  የሳንባ በሽታ ያለባቸው የኩላሊት በሽታ እና የመከላከል አቅማቸው የተዳከመ
  • ተጨማሪ ምክሮችን ይመልከቱ

እንዴት ነው COVID-19 (ኮቪድ-19 ኮሮና ቫይረስ) የሚሰራጨው? ምልክቶቹስ ምንድን ናቸው ስርጭቱንስ እንዴት መከላከል እችላለሁ?

COVID-19 (ኮቪድ-19 ኮሮና ቫይረስ) የሚተላለፈው በሚከተለው  ሁኔታ ነው: -

  • የመተንፈሻ ነጠብጣቦችን የሚፈጥር ሳል እና ማስነጠስ
  •  የግል ንክኪ ፣ ለምሳሌ እንደ መነካካትና እጅ እንደመጨባበጥ፣
  • ቫይረሱ ያለበትን ቦታ ወይም ዕቃ  በመንካት

ምልክቶች:·

  • ትኩሳት·
  • ሳል
  • የትንፋሽ እጥረት
  • የከፋ ከሆነ ደግሞ፣ ኒሞንያ (የሳንባ ምች)

አንድ ሰው COVID-19 (ኮቪድ-19 ኮሮና ቫይረስ) ካለበት ምን ይሆናል?

ብዙዎች ከዚህ ኢንፌክሽን ይድናሉ፤ ወደ 80 ከመቶ የሚጠጉት መካከለኛ ወይም መለስተኛ ሊኖራቸው ይችላል። የታመሙ ሰዎች ራሳቸውን ከሌሎች ለይተው በቤታቸው እንዲያገግሙ ይመከራል። እነዚህ ግለሰቦች ምልክቶቹ እየባሱ ከሄዱባቸው ወድ ሃኪማቸው ወይም ክሊኒክ መደወል አለባቸው። ኮቪድ-19  አዲስ በሽታ በመሆኑ የሚፈውስ ልዩ መድሃኒት የለውም። ሆኖም ግን ኮቪድ-19  ያለባቸው ሰዎች የበሽታውን ክብደት ለመቀነስ የህክምና እርዳታ ማግኘት አለባቸው።

ጥቂቶች የኮቭድ-19 (ኮሮና ቫይረስ) ኢንፈክሺን ወደከፋ በሽታ በአንዳንድ ሁኔታዎችም ወደ ሞት ሊመሩ ይችላሉ፣  አንድሰው ከኮቪድ-19 የተነሳ  በጣም የከፋ በሽታ ካለው ሆስፒታል ሊገባ ይችላል። አዛውንትና ቀድሞውኑ የጤና ችግር ያለባቸው ለከፋ በሽታ የመጋለጥ እድላቸው ሰፊ ነው።  ለምሳሌ ቀደሞውኑ  ያሉ የጤና ችግሮች የሚከተሉት ናቸው፦ ካንሰር፣ የስኳር በሽታ፣ የልብ በሽታ፣ ሲኦፒዲ እና የስውነታችን ጀርሞችን የመከላከል አቅም ላይ ተጽእኖ የሚያመጡ።

እራሴን እና ሌሎችን ለመጠበቅ ምን ማድረግ እችላለሁ?

COVID-19 (ኮቪድ-19 ኮሮና ቫይረስ) ን ለመከላከል ክትባት የለም። በመሆኑም ከትንፋሽ ጋር የተያያዙ እንደ ጉንፋን፣ፍሉ እና COVID-19 (ኮቪድ-19 ኮሮና ቫይረስ) ን  በሽታዎች ስርጭት ለመቀነስና ለመከላከል  የተሰጡትን ምክሮች በመከተል  በየቀኑ የመከላከያ እርምጃዎችን መውሰድ

  • ማንኛውም  ቴለዎርክ ሰራተኛም ይህንን ሊተገብር ይገባል
  • ወደውጭ መውጣትዎን አስፈላጊ ጉዳይ ብቻ ይ የቤተሰብዎ አባል ካልሆነ ሰው ፮ ጫማ ያህል ራቅ ማለትዎን ያረጋግጡ፤
  • በቡድን  ከመሰብሰብ ይታቀቡ፤
  •  ቢያንስ ለ 20 ሰከንዶች ያህል እጆችን ሞቅ ባለ ውሃና ሳሙና አዘውትሮ መታጠብ፡፡
  • ውሃና ሳሙና ከሌለ ቢያንስ 60 ከመቶ የሆነ አልኮሆል ነክ የእጅ ማጽጃ ይጠቀሙ ፡
  • በተደጋጋሚ የሚነኩ እቃዎችንና ቦታዎችን መደበኛ የጽዳት አሰራሮችን በመጠቀም ማጽዳት፤
  • ሲያስሉና ሲያስነጥሱ በሶፍት፣ በኮሌታዎ ወይም በክርንዎ ይሸፈኑ።
  • ዓይንዎን፣አፍንጫዎናፍዎን ከመንካት ይቆጠቡ፤
  • ከታመሙ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ አያድርጉ፡፡
  • ካመምዎ መድሃኒት ለማግኘት ካልሆነ በቀር በቤትዎ ይቆዩ፤ ማንኛውንም በሽታ ለአለቃዎ ያሳውቁ።

በ COVID-19 (ኮቪድ-19 ኮሮና ቫይረስ) ታማሚ እንደሆንኩ ካሰብኩ ምን ማድረግ ይኖርብኛል?

በቅርቡ አለማቀፍ ጉዞ አድርገው ከሆነ ወይም የ COVID-19 (ኮቪድ-19 ኮሮና ቫይረስ) ህመምተኛ ከሆነ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ አድርገው ከነበረና ትኩሳት ሳል ወይም የመተንፈስ ችግር  ካለብዎ ወዲያውኑ የህክምና እንክብካቤ ይፈልጉ።  እነዚህን እርምጃዎች ይከተሉ፡

  • በቤትዎ ካሉ ሌሎች ሰዎች ራስዎን ያግሉ
  • ቢቻል ከቤት እንስሳትና ከእንስሳት  ጋር ያለዎትን ግንኙነት ይመጥኑ
  • ከመሄድዎ በፊት ለዶክተርዎ ወይም ድንገተኛ ክፍል ይደውሉ፤
  • ቅርብ ጊዜ ተጉዘው ከሆነ እና(ከቤተሰብዎ ውስጥ ካሉ ሰዎች ጋር) የቅርብ ንክኪ አድርገው ከሆነ ይንገሯቸው፤
  • ጭንብል ካለዎ ያጥልቁት፣ የፊት ጭንብል ወይም ቀላል የቀዶ ጥገና የፊት ጭንብል ተገቢ ይሆናል።.

 ሰዎች ለኮ COVID-19 (ኮቪድ-19 ኮሮና ቫይረስ) እንዴት ሊመረመሩ ይችላሉ?

የ COVID-19 (ኮቪድ-19 ኮሮና ቫይረስ) መመርመሪያ መሳሪያ በገበያ ላይ የለም። COVID-19 (ኮቪድ-19 ኮሮና ቫይረስ) እንዳለባቸው የሚጠረጥሩ ሰዎች የጤና እንክብካቤ አቅርቦት የሚያደርግላቸውን መገናኘት ይኖርባቸዋል። ህመምተኞች የሚያሳይዋቸው  የኮቪድ19 ምልክቶች መሆናቸውን በማጣራት ወደ ላብራቶሪ ምርመራ ይልኯቸዋል።

ሀኪምዎ ወይም የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎ ምልክቶችዎን በመገምገም የኮቪድ-19 ቫይረስ ምርመራ ማድረግዎት ተገቢ እንደሆነ ያጣራል። የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎት COVID-19 (ኮቪድ-19 ኮሮና ቫይረስ) ከጠረጠረ ምርመራውን ከንግድ ላብራቶሪዎች ጋር ወይም የመንግስት የህዝብ ጤና ላብራቶሪዎች ጋር ያቀናጃል። አንዳንድ የንግድ ላብራቶሪዎች ውጤትን ማጤንና ሪፖርት ለታማሚው ወይም ምርመራውን ላዘዘው ተንከባካቢ ማቅረብ ችሎታው ቢኖራቸውም ፣ በአሁኑ ጊዜ ምርመራውን የማጤን ስራ እንጂ ከበሽተኞች በቀጥታ ናሙና አይወስዱም። የሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤናና የሕዝብ አገልግሎቶች የበሽታ ቁጥጥር ቢሮ ነርስ ለማናገር እባክዎ በ 240-777-1755 ይደውሉ።

መላው ህዝብ ጭንብል ማጥለቅ ይኖርበታል?

ሲዲሲ (CDC)  ማህበራዊ ርቀትን ለመተግበር አስቸጋሪ በሆነበት ስፍራ ሁሉ የፊት መሸፈኛ ማጥለቅን ያዛል፤ ከሁለት ዓመት በታች ለሆኑ ልጆችና የመተንፈስ ችግር ላለባቸው ግለሰቦች ግን አይመከርም። የጨርቅ የፊት ሽፋኖች ዓላማ ጤናማነት የሚሰማቸው ግን COVID-19 (ኮቪድ-19) ያለባቸው ሰዎች ባለማወቅ በሌሎች ሰዎች ዙሪያ በሚሆኑበት ጊዜ የመተንፈሻ ጠብታዎችን እንዳያሰራጩ ለመከላከል ነው ፡፡ የፊት ጨርቅ ሽፋኖች እንደ የቀዶ ጥገና ጭንብል እና የ N95 የመተንፈሻ ጭንብል ሽፋን አንድ አይነት የጥበቃ ደረጃ የማይሰጡ መሆናቸውን አፅንዖት ሊሰጥ ይገባል ፡፡ የቀዶ ጥገና ጭምብል እና የN95 የመተንፈሻ ጭንብል ለጤና ማእከልት መስጫና ለጤና እንክብካቤ ግንባር ቀደም ሠራተኞች ተጠብቀው መቀመጥ ይኖርባቸዋል ፡፡ የፊት መሸፈኛ ልብስ ማሟላት ያለባቸው:-

  • ልከኛና ነገር ግን በፊትዎ ላይ ምቹ  መሆን አለባቸው
  • በማሰሪያና በጆሮ ማጥለቂያ በደንብ ይጠበቅ
  • ድርብርብ ጨርቆችን ያካቱ
  • ያለምንም ችግር መተንፈስ የሚፈቅዱ
  • የሚታጠቡና ሳይጎዱ ወይም ቅርጻቸውን ሳይቀይሩ በማሽን መድረቅ የሚችሉ

የፊት ሽፋን የሚያደርጉ ከሆነ፣ በየጊዜውማጠብ አስፈላጊ ነው። በማሽን ማጠብ ተቀባይነት ያለው የጽዳት ዘዴ ሆኖ ይቆጠራል፣ ግለሰቦች የፊት ሽፋናቸውን ሲያወልቁ  አይኖቻቸውን፣ አፍንጫቸውን እና አፋቸውን እንዳይነኩ መጠንቀቅ ይኖርባቸዋል፣ ካወለቁ በኋላም ፈጥነው ኢጆቻቸውን መታጠብ ይኖርባቸዋል።

የራስዎን የጨርቅ ጭንብል መስራት ከፈለጉ  እንዴት መስራት እንድሚችሉ መመሪያዎችና ቪዲዮዎች እነሆ፤

ለ COVID-19 (ኮቪድ-19 ኮሮና ቫይረስ) እንዴት በበለጠ መዘጋጀት እችላለሁ?

ያለ መድሃኒት ማዘዣ በፋርማሲ ውስጥ ሊገዙዋቸው የሚችሉ መድሃኒቶች ይኑርዎ ሌላም የጤና አቅርቦቶች፣  እንደ ህመም ማስታገሻ፣ የሆድ መድሃኒቶች፣ ያሳልና የጉንፋን መድሃኒቶች፣ ኤሌክትሮላይት ያለበት ፈሳሽ እና ቫይታሚኖች በእጅዎ ይኑርዎት።  ድንገት ቢያምዎ እስኪሻልዎ እቤት መቆየት ካለብዎ፣ የሙቀት መለኪያ፣ ሶፍት እና የእጅማጽጃ ይኑርዎ፣ ከቤተሰብ አባላትዎ እና ከወዳጆችዎ ጋር ቢያማቸው እንዴት እንክብካቤ ሊያደርጉላቸው እንደሚችሉ ወይም   በቤትዎ እንክብካቤ እንዲደረግላቸው ምን እንደሚያስፈልግ ያውሯቸው። ለሁለት ሳምንታት የሚበቃ የውሃ እና ምግብ አቅርቦት በቤትዎ ይኑርዎ።

የቤተሰብ ጉዞዬን መሰረዝ አለብኝ? 

በአሁኑ ጊዜ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል (ሲዲሲ) ተጓዦች ወደ ቻይና፣ ኢራንና ደቡብ ኮሪያ አላስፈላጊ ጉዞዎችን ሁሉ እንዲያስወግዱ እያስጠነቀቀ ነው። በተጨማሪም አዛውንት በተለይም ስርበሰደድ የጤና ችግር ያላቸው ወደ ጃፓን የሚደረግ አላስፈላጊ ጉዞን እንዲያስወግዱ በማስጠንቀቅ ላይ ነው። ብዙ ሃገራት በህዝባቸው መሃል የኮቪድ-19  መስፋፋትን እየዘገቡ ሳለ፣  በጉዞ አማካሪ መዝገብ የሚጨመሩት ሃገራት ቁጥር ማሻቀቡ አይቀርም። የጉዞ ምክሮችን በ ሲዲሲ ድረ ገጽ ይመልከቱ።

ማወቅ ያለብኝ ሌላ ነገር አለ?

የየትኛውንም አገር ሰው ከዘር እና የዘር ጀርባ ታሪክ ጋር ግንኙነት ባለው መልኩ አያግሉ። በቅርቡ ወደ ቻይና ወይም ጉዳት ወደደረሰባቸው አካባቢዎች ያልተጓዙና ከኮቪድ-19  ታማሚ ጋር የቅርብ ንክኪ ያላደረጉ ከእርስዎ ይልቅ ከፍተኛ አደጋ ውስጥ ያሉ አይደሉም፤ ቫይረሶች የተለዬ  ህዝብን፣ ጎሳዎችን እንዲሁም ዘርን ለይተው ኢላማ አያደርጉም። መረጃዎችን አዘውትረው ይከታተሉ፤ መረጃዎችንም  ከታመኑ ከሆኑ ምንጮች ብቻ  ያግኙ፤ ከአፈታሪክ፣ ከወሬ እና ከተሳሳቱ መረጃዎች  እንዲሁም በኦንላይን እና በተለያየ ቦታ የተጭበረበረ መረጃ ከሚያናፍሱ ይጠንቀቁ። ከታመነ ምንጭ ካልሆነ በስተቀር በሶሻል ሚዲያ የሚናፈሱ የጤና መረጃዎች ብዙ ጊዜ የተዛቡ ናቸው።