ኮቪድ-19 የምግብ ግብዓቶች

311 (240-777-0311) በመደወል የምግብ አቅርቦት ጥሪ ማእከል ይጠይቁ። በ24 ሰአት ዉስጥ በመረጡት ቋንቋ የስልክ ጥሪዎት ይመለስሎታል። እርዳታ ለማግኘት የግል መለያ መረጃ አያስፈልግም።


በአማርኛ አገልግሎቱን ማግኘት ከፈለጉ, እባክዎት ብርቱካን አስረስን ከቴስ የማህበረሰብ ድርጊት ማእከል በ240-773-8252 ይደዉሉ ወይም ኢሜል ይላኩላት Birtucan.Assres@montgomerycountymd.gov.

ምግብ የማከፋፈል ዝግጅት


በአካባቢዎ ያሉ የምግብ እርዳታ ጣቢያዎች

በአካባቢዎ ያሉ የምግብ አቅርቦት አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን ለማግኘት የምግብ እርዳታ ማገናዘቢያ ካርታ ይጠቀሙ :: ካርታው ወደ ምግብ አቅራቢዎቹ ይመራዎታል። አድራሻዎን በማስገባት በቅራቢያዎ ያሉ አቅራቢዎችን ማግኘት ይችላሉ። የተለዩ ቋንቋዎችን የሚናገር አቅራቢዎች፤  የማድረስ አገልግሎትየሚሰጡ፣ ወይም የተለዬ አገልግሎት የሚሰጡትን መፈለግ ያስችልዎታል። እነዚህን ገጽታዎች ለማግኘት "ማጣሪያዎችን ያሳዩ" የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ

የምግብ አቅርቦት ጥሪ ማእከል

311 (240-777-0311) በመደወል የምግብ አቅርቦት ጥሪ ማእከል ይጠይቁ። በ24 ሰአት ዉስጥ በመረጡት ቋንቋ የስልክ ጥሪዎት ይመለስሎታል። እርዳታ ለማግኘት የግል መለያ መረጃ አያስፈልግም።

የሰለጠነ የመረጃ ባለሙያ ስለነፃ ምግብ እና የሸቀጣእሸቀጦች አቅርቦትና ስናፕ (ፉድ ስታምፕ) በአካባቢዎ የሚገኙ የምግብ አቅራቢዎች እና ስለ ሞንትጎመሪ ካዉንቲ ሌሎች መረጃዎችን በሚመለከት መረጃ ይሰጡዎታል።

ለህፃናት ምግቦች

ለልጆች ነፃ ምግብ ለማግኘት  የሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ትምህርት ቤቶችን ድረ ገፅን ይጎብኙ።


ምግብ ጠና ላሉ አዋቂዎች

ተጨማሪ የተመጣጠነ ምግብ ድጋፍ ፕሮግራም ፣ SNAP (በመደበኛነት ፉድ ስታምፕ በመባል ይታወቃል)

SNAP (ስናፕ) (ከዚህ ቀደም ፉድ ስታምፕ ተብሎ የሚጠራው) ለማመልከት እዚህ ጠቅ ያድርጉ ፡፡ በዚህ ወረርሽኝ ጊዜ ልዩ ጥቅማጥቅሞች ይገኛሉ ፣ ይህም አነስተኛ ጥቅማጥቅሞችን እና የትምህርት ቤት እድሜ ላላቸው ልጆች ጭማሪ ይደረጋል።

ለስናፕ (SNAP) ማመልከቻዎ እገዛ ያግኙ

  • የሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና የሰብአዊ አገልግሎቶች ክፍል የ SNAP ማመልከቻዎችን ለማከናወን ይረዳል፡፡ 240-777-1003 ላይ ይደውሉ።
  • ለሜሪላንድ የረሃብ መፍትሄዎች የስናፕ (ፉድ ስታምፕ) ማመልከቻዎችን በተመለከተ የስልክ አገልግሎት በመስጠት ሊረዳዎት ይችላል፤ 866-821-5552 ላይ ይደውሉ።
  • Catholic Charities SHARE Program – Call 301-864-3115/1-800-21-SHARE (toll free)
  • Spanish Catholic Center – Call 301-740-2523 (Gaithersburg) or 301-434-8985 (Wheaton)

ተጨማሪ የ SNAP(ስናፕ) መረጃ፡


ሴቶች ፣ህፃናትና ልጆች (WIC)

WIC (ድብሊው አይ ሲ) ጤናማ ምግቦች ፣የጤና ትምህርት፣ ለጡት አጥቢዎች እርዳታ እና ሌሎችም ከክፍያ ነጻ የሆኑ አገልግሎቶች ለነፍሰጡሮችና ከወሊድ በኋላ ላሉ ሴቶች፣ መስፈርቱን ለሚያሟሉ ህፃናት እና ልጆች ያዘጋጃል።

ለ WIC (ድብሊው አይ ሲ) ፕሮግራም ለማመልከት የWIC (ድብሊው አይ ሲ) ድረ ገፅን ይጎብኙ ወይ


ም 301-762-9426 ላይ ይደውሉ።

የአረጋዉያን የአመጋገብ ፕሮግራም

የአረጋዉያን የአመጋገብ ፕሮግራም በየሳምንቱ ሰባት የቀዘቀዙ ምግቦችን በአረጋዉያን የምግብ ማእከል (Senior Meals Sites). ለተመዘገቡ ተሳታፊዎች ይሰጣል። እነዚህ ማእከሎች የሚገኙት ዳማስከስ (Damascus), ሆሊደይ ፓርክ (Holiday Park), ሎንግ ብራንች (Long Branch), Schweinhaut, ዊተን (Wheaton) ኖርዝ ፖቶማክ (North Potomac) ዋይት ኦክ (White Oak), and ሮክቪል የአረጋዉያን ማእከል (Rockville Senior Centers) and ቦህረር ፓርክ (Bohrer Park)።

ተሳታፊዎች በራሳቸዉ ወይም ጓደኛ /ቤተሰብ /የበጎ ፈቃደኛ ምግባቸዉን መዉሰድ ይችላሉ። በአንዳንድ ሁኔታወች ምግብ ምግብ በመዝናኛ ክፍል ሰራተኞች ሊሰጥ ይችላል።

ለምግቦቹ ምንም የተወሰነ ዋጋ የለም, ነገር ግን የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች አገልግሎቱን ለሌሎች ለማገዝ በበጎ ፈቃደኝነት መዋጮ voluntary contribution እ ንደሚያደርጉ ተስፋ ይደረጋል።

60 አመት እና በላይ የሆኑ የካዉንቲዉ ነዋሪዎች ለዚህ ፕሮግራም ብቁ ናቸዉ። የተሳታፊዉ ባለቤት ወይም አብሮ የሚኖር የአካል ጉዳተኛ ግለሰብ ለአገልግሎቱ ብቁ ናቸዉ።v

ፕሮግራሙ አዳዲስ ጥያቄዎችን ይቀበል እንደሆነ ለማየት ለእርስዎ ቅርብ የሆነዉን የአረጋዉያን ማእከል ያነጋግሩ። ስለአረጋዉያን ተጨማሪ መረጃ ይመልከቱ See more information about the Senior Nutrition Program, ስለእያንዳንዱ የአረጋዉያን ማእከል መረጃን በመጨመር።


ምግብ የማድረስ አገልግሎት

ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ድርጅቶች ለራሳቸው ምግብ መግዝት ላልቻሉት ወይም ለማዘጋጀት ለማይችሉት ምግብ የማድረስ አገልግሎት ይሰጣሉ


የ ሸቀጣ ሸቀጥ አቅርቦት አማራጮች

ሸቀጣ ሸቀጦችን ለመግዛት አቅም ለሌላቸው፣ የሚከተሉት ድርጅቶች የምግብ እርዳታ መስጠት እና ምግቡን ወደ ግለሰቡ ቤት ያደርሳሉ


ማድረስ የሚችሉ የምግብ እርዳታ አቅራቢዎች

የሸቀጣ ሸቀጦችን ለመግዛት አቅም ላላቸው ግን የትራንስፖርት እገዛ ለሚያስፈልጋቸው ፣ የሚከተሉትን ፕሮግራሞች የሸቀጦች ሸቀጣ ሸቀጦችን ወደ ሰው ቤት በማድረስ ሊረዱ ይችላሉ ፡

አገልግሎት አቅራቢዎቹ ምናልባት በአካባቢ፣ በዕድሜ፣ በባህል ወይም ልዩ ለሆነ ህዝብ አባልነት ውሱን ሊሆን ይችላል።


ዕርዳታ ለመለገስና የበጎ ፈቃድ አገልጋይ

ለምግብ ዕርዳታ ግብዓት የሚሆኑ ነገሮችን ፣ ገንዘብን ወይም ጊዜን መለገስ በተመለከተ መረጃ ለማግኘት የሞንትጎመሪ ካውንቲ በጎ ፈቃደኞችን ማእከልን ያነጋግሩ።