በሞንትጎመሪ ካውንቲ የኮቪድ-19 ምርመራ እንዴት አገኛለሁ?

ስለ ምርመራዎቻችን

ምርመራው ነጻ ነው። ኢንሹራንስ ካለዎት መረጃዎትን እንጠይቅዎታለን ነገር ግን ምንም አይነት የጋራ ክፍያ ወይም ተቀናሽ የለም። የምንሰበስበውን መረጃ አያያዝ በተመለከተ የመረጃ አያያዘ ተግባራዊነት ማሳወቅያን ይመልከቱ

የመንግስት መታወቂያ ወይም የዶክተር ትእዛዝ አንጠይቅም።

በሞንትጎመሪ ካውንቲ ለሚኖር፣ ለሚሰራ ወይም በመደበኛነት ለሚጎበኝ ለማንኛውም ሰው ምርመራ እንሰጣለን።

በሁሉም ዕድሜ ውስጥ ያሉ ሰዎችን እንመረምራለን። ህጻናትን ይዘው ከመጡ፤ ህጻናቱ ሲመረመሩ እርስዎ እንዲያግዙዋቸው ልንጠይቅ እንችላለን።

የእኛ ክሊኒኮች በአፍንጫ የሚደረጉ ምርመራዎችን ይሰጣሉ። ናሙናውን እራስዎ ይወስዳሉ። ምርመራዎቹ molecular ናቸው፣ በተጨማሪም PCR ተብለው ይጠራሉ። እነዚህ ምርመራዎ የኮቪድ -19 ቫይረስ ዘረመል አይነት የሚለዩት polymerase chain reaction (PCR) የተባለ የላብራቶሪ ዘዴን በመጠቀም ነው። በክሊኒካችን የ antibody ምርመራ አንሰጥም።

የምርመራ ውጤቶትዎ

በካውንቲ ሚተዳደሩ ክሊኒኮች የምርመራ ውጤቶችን ለማግኘት ከ2 እስከ 3 ቀናት ይወስዳል። ውጤትዎ በኢሜይል ወይም የጽሁፍ መልእክት ይደርስዎታል።

በተጨማሪም የምርመራ ውጤትዎን በኦንላይን ማየት ይችላሉ።

የእርስዎ ምርመራ በዚህ ክሊኒክ ከሆነ የምርመራ ውጤትዎን በኦንላይን ላይ ይመልከቱ
በካውንቲ የሚደገፍ ክሊኒክ የ20/20 GeneSystems የምርመራ ውጤቶችን ይመልከቱ
አጋር ክሊኒክ የ CIAN የምርመራ ውጤቶችን ይመልከቱ (ፒዲኤፍ)
ሜሪላንድ SoccerPlex የ SoccerPlex ውጤቶችን ይመልከቱ
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የመንግስት ሰራተኛ ክሊኒክ የካውንቲ ሰራተኛ ክሊኒክ የምርመራ ውጤቶችን ይመልከቱ

ከምርመራ በኋላ በ 3 ቀናት ውስጥ ውጤትዎን ካልተቀበሉ የምርመራ ጣቢያዎን ያነጋግሩ።

በህጻናት እንክብካቤ መስጫ ተቋማት፣ ትምህርት ቤቶች፣ ካምፕ፣ ወዘተ የኮቪድ-19 ፖዘቲቭ ጉዳይ ሪፖርት ለማድረግ ለኮቪድ-19 የጥሪ ማእከል በ 240-777-2982 ይደውሉ።

MOCO የኮቪድ-19 ምርመራ ነፃ ፣ ቀላል ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ። www.mococovidtesting.org - የዶክተር ትእዛዝ አያስፈልግም። የምርመራ ቦታዎች። የኦንላይን የምርመራ ውጤቶች። የቤት ውስጥ ምርመራ አማራጮች አሉ።

የካውንቲ ኮቪድ-19 ምርመራ ክሊኒኮች

አረጋውያን እና አካል ጉዳተኞች ፤ ወደ ኮቪድ-19 መመርመርያ ክሊኒክዎ ነጻ መጓጓዣያግኙ።