በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች ስለ ክትባቱ

በዚህ ገጽ ላይ

በክትባቶች ዙሪያ ስለሚከሰቱት ነገሮች ሁሉ እንዴት መከታተል እችላለሁ?

ለኢሜል / ለአጭር የጽሑፍ መልእክት ይመዝገቡ። ከኮቪድ-19 ክትባቶች ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ወቅታዊ መረጃዎች እና ለጥያቄዎች መልስ ለመስጠት እነዚህን ዝመናዎች እንዲሁም የእኛን ድህረገፅ ፣ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን እና ሌሎች የመገናኛ መስመሮችን እንጠቀማለን ፡፡

ቅድመ ምዝገባ እና ቀጠሮዎች

እኔ ያለሁበትን የቅድሚያ ቡድን እንዴት ማወቅ እችላለሁ?

Vቅድሚያ የሚሰጠውን የቡድን ዝርዝሮች ይመልከቱ። ቅድሚያ የሚሰጡት ቡድኖች የተወሰኑት በአንጻራዊነት የመጋለጥ አደጋን ወይም አንድ ሰው ኮቪድ-19 ከያዘው ከባድ በሽታ የመያዝ እድልን መሠረት በማድረግ ነው ፡፡

በዚያ ቡድን ውስጥ ያሉ ሰዎች ጤንነታችንን እና ደህንነታችንን ስለሚጠብቁ እና ሥራዎቻቸው ለአደጋ ተጋላጭ ስለሚያደርጋቸው የ 1ኤ ቡድንን ማጠናቀቅ የካውንቲው ሃላፊነት መሆኑን ግዛቱ በድጋሚ አስታውቁዋል። እነሱ እንዲታመሙ የመተው አቅም የለንም ፡፡ በቡድን 1 ኤ ውስጥ ካሉ ሰዎች በኋላ ቀጣዩ የ1 ቢ ቡድን ዕድሜያቸው 75 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎችን ያጠቃልላል ፡፡ ስቴቱ ያንን ቡድን እስኪጨርስ ድረስ ዕድሜያቸው ከ 75 እና ከዚያ በላይ የሆናቸው የነዋሪዎች ቡድን ለካውንቲያችን ቅድሚያ እንደሚሆኑ ይጠብቃል ፡፡ የካውንቲ ጤና እና ሰብዓዊ አገልግሎት መምሪያ ክትባቶች በተመደበለት መጠን ያን ጊዜ ይወስዳል ፡፡

ኮምፒተር ከሌለኝ ምን ማድረግ አለብኝ?

ለመመዝገብ ብቁ ከሆኑ እና ኮምፒተር ማግኘት ካልቻሉ የቤተሰብ አባልዎን ወይም ጓደኛዎን ኦንላይን ቅጹን እንዲሞሉ እንዲያግዞት ይጠይቁ ፡፡ እንዲሁም ለእርዳታ ወደ ቅድመ ምዝገባ የእገዛ መስመር በ 240-777-2982 መደወል ይችላሉ። ሠራተኞች ለደዋዮች በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽ አገልግሎት ይሰጣሉ ፡፡ የእርዳታ መስመር ከሰኞ እስከ አርብ ከጥዋቱ 9 ሰዓት እስከ ማታ 5 ሰዓት ክፍት ነው፡፡ 

ስለ ክትባት እና ስለ ኮቪድ-19 አጠቃላይ ጥያቄዎች ካለዎት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዎቱ 8 ሰዓት እስከ ማታ 6 ሰዓት በ 240-777-2982, ይደውሉ ፡፡

የኢሜል አድራሻ ወይም የጽሑፍ መልእክት የሚቀበል ስልክ ከሌለዎት ቀጠሮ ለመያዝ ተራዎ ሲደርስ እንደውልልዎታለን ፡፡

የኮቪድ-19 ክትባት ጣቢያ እንዴት ማግኘት እችላለሁ?

በካውንቲው በሚተዳደሩ ክሊኒኮች ውስጥ ቀጠሮ ለመያዝ የኛን የክትባት መነሻ ገጽ አገናኝ ይመልከቱ ፡፡

ለቀጠሮ ቅድመ ምዝገባ ካደረጉ፡ እኛ ለእርሶ ቀጠሮ ለመያዝ ስናገኝዎት ለነዚያ ቀኖች ያሉንን ቦታዎች እንነግሮታለን ፡፡

በዲ.ኤች.ኤች.ኤስ ከሚሰሩት ክሊኒኮች በተጨማሪ ሆስፒታሎች እና በርካታ የህብረተሰብ አጋሮች የ ኮቪድ-19 ክትባቶችን ለህዝብ አቅርበዋል ፡፡ በአቅራቢያዎ ያሉ ቦታዎችን ይፈልጉና ቀጠሮ ይያዙ

ለአርበኞች በተለየ ሁኔታ የክትባት ቀጠሮዎች አሉ?

አዎ ፣ VA(ቪኤ) የህክምና ማዕከላት ክትባት ይሰጣሉ በ VA(ቪኤ) የጤና እንክብካቤ የተመዘገቡ አንጋፋዎች።

የትኛውን ክትባት እንደምወስድ መምረጥ እችላለሁ?

በአሜሪካ ውስጥ ጥቅም ላይ እንዲውሉ የተፈቀዱ ሁሉም ክትባቶች ደህና እና ውጤታማ እንደሆኑ ተረጋግጠዋል ፡፡

አብዛኛዎቹ የክትባት ጣቢያዎች የሚጠቀሙት አንድ የክትባት ዓይነት ብቻ ስለሆነ የትኛውን ክትባት እንደሚወስዱ መምረጥ አይችሉም ፡፡ የትኛውን ክትባት ቢወስዱ የጤንነትዎን ለበሽታ ተጋላጭነት በእጅጉ ይቀንሰዋል ፡፡

ሦስቱን ክትባቶች የሚያነፃጽረዉን ግራፊክ ይመልከቱ ፡፡

ስለ ሁለተኛው ክትባቶችስ?

የሞደርና እና ፋይዘር ክትባቶች ሁለተኛ መጠን ያስፈልጋቸዋል ፡፡ የጆንሰን እና ጆንሰን ክትባት አንድ መጠን ይፈልጋል ፡፡

የመጀመሪያ ክትባትዎን በሞንጎመሪ ካውንቲ ከሚተዳደር ክሊኒክ ከተቀበሉ፤
ሁለተኛው የክትባት መጠንዎ ከመድረሱ ከ 4 እስከ 7 ባሉት ቀናት ቀጠሮ ለመያዝ እናሳዎቅዎታለን ከቀጠሮ መያዝ ግብዣ ጋር ፡፡ ኢሜሉ ከ [email protected] ይመጣል ፡፡ እንዲሁም ከቅድመ-ዝግጅት ስርዓት(PrepMod ) ማስታሻዎችን ማግኘትም ይችላሉ ፡፡

ከመጀመሪያው መጠን ጋር በተቀበልኩበት የክትባት ካርድ ምን ማድረግ አለብኝ?

የኮቪድ-19 ክትባት የሚወስድ እያንዳንዱ ሰው የ የክትባት መዝገብ ካርድ አግኝቷል። ካርዶቹ የሚሰጡት በበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከላት ሲሆን እንደ የግል ክትባት መዝገብ ሆነው ያገለግላሉ ፡፡ ካርዱ የመጀመሪያ መጠንዎን የተቀበሉበትን ቀን እና ምን ክትባት እንደወሰዱ ይዘረዝራል ፡፡ እንደ ፋይዘር ወይም ሞደርና ያሉ ባለ ሁለት ክትባት መጠን ከተቀበሉ የመጀመሪያ ክትባትዎ ቀን የሁለተኛው መጠንዎ መቼ እንደሚሆን አጠቃላይ ግንዛቤ ይሰጥዎታል (ከሶስት ሳምንት በኋላ ፋይዘርን ከተቀበሉ እና ከአራት ሳምንታት በኋላ ሞደርናን ከተቀበሉ) .

ካርዱን መቃኘት (እስካን ማድረግ) ወይም ፎቶግራፍ ማንሳት ይመከራል ፡፡ ዋናውን በቀላሉ ሊደርሱበት በሚችሉበትና ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ ያኑሩ። የግል መለያ መረጃን ስለያዘ የካርድ ፎቶዎችን በማህበራዊ መረቦች ከመለጠፍ ይጠንቀቁ ፡፡ ለመለጠፍ ከወሰኑ መረጃውን ማደብዘዝን ከግምት ያስገቡ ፡፡

ስለ ኮቪድ-19 ክትባት

ክትባቱ እንዴት ነው የሚሰራው?

የምንቀበላቸው የ ኮቪድ-19 ክትባቶች ኤምአርኤንኤ ክትባቶች ናቸው። የደከመ ወይም የማይሰራ ጀርም ወደ ሰውነታችን በመክተት የመከላከል አቅምን ከሚፈጥሩ ብዙ ክትባቶች በተለየ መልኩ፣ ኤምአርኤንኤ ክትባቶች የሚያደርጉት ህዋሶቻችንን የመከላከል አቅም የሚፈጥርን ፕሮቲን ወይም የፕሮቲን ቁራጭ እንዴት ማምረት እንደሚችሉ ነው። ክትባቱ የመከላከል አቅምን ሲፈጥር፣ ሰውነቶቻችን አንቲቦዲዎችን(ፀረ እንግዳ አካላት) በመፍጠር በእውነተኛው ቫይረስ ስንጋለጥ በበሽታው ከመበከል ይጠብቁናል።

ለአብዛኛው ኮቪድ-19 ክትባቶች፣ ክትባቱ ሁለት ጊዜ መውሰድ ይጠይቃል። የኦንላይን አገልግሎት የሆነው ፕሬንሞድን በመጠቀም ቀጠሮዎችን ማስያዝ እና ሰዎች ሁለተኛውን የክትባት መውሰጃ መቼ እንደሆነ ማስታወሻዎችን ለመላክ ጭምር እንጠቀምበታለን።

ተጨማሪ መረጃዎች

የኮቪድ-19 ክትባትን ሁሉም ማግኘት አለበትን?

አዎ። ኮቪድ-19 የሚያጠቃቸው ላይ ያለው ጫና ይለያያል፣ ከአነስተኛ ራስ ምታት እስከ የከፋ በሽታ እንዲሁም ሞት። መከተብ እርስዎን ሲጠብቅ፣ እንዲሁም በዙሪያዎ ያሉ ሰዎችን ከ ኮቪድ-19 በከባድ ህመም ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችንም በተጨማሪ ለመጠበቅ ይረዳል። ምንም እንኳን በ ኮቪድ-19 መያዝ የተወሰነ የተፈጥሮ መከላከል ሊሰጥ ቢችልም፣ ይህ መከላከል ለምን ያህል ጊዜ ሊቆይ እንደሚችል እስካሁን አይታወቅም።

ቀድሞውኑ ኮቪድ-19 ቢኖረኝስ? አሁንም ከትባት መውሰድ ያስፈልገኛል?

ሲ.ዲ.ሲ ቀደም ብለው በኮቪድ-19 ለተያዙ ሰዎች አሁንም ክትባት እንዲወስዱ ይመክራል ፡፡ ክትባቱ የበለጠ የበሽታ መከላከያ ምላሽ ሊሰጥ ይችላል ፣ ይህም ለወደፊቱ ከኮሮና ቫይረስ ጋር ለመዋጋት ሰውነትን በተሻለ ያዘጋጃል ፡፡ በተጨማሪም ፣ ከኮቪድ-19 ካገገሙ በኋላ እንደገና ከመታመም ምን ያህል ጊዜ እንደሚጠበቁ ባለሙያዎች እስካሁን ድረስ አያውቁም ፡፡ ቀድሞውኑ ከኮቪድ-19 ካገገሙ በድጋሜ በቫይረሱ ሊጠቁ ይችላሉ - ምንም እንኳን አልፎ አልፎ ቢሆንም ፡፡

የክትባቱን የቅድሚያ ስርጭት ማን ይወስናል?

ሲዲሲ ስለ ክትባቱ አግባብ ያለው ምደባ እና ስርጭት ውሳኔዎችን ያደርጋል፤ ይህም ከመከላከል አቅም አሰራር ልምዶች አማካሪ ኮሚቴ (ኤሲአይፒ) እና የብሄራዊ የሳይንስ፣ የምህንድስና፣ እና መድሃኒት አካዳሚዎች በሚገኝ አስተያየት ላይ ይሆናል። ምንም እንኳን የስቴት እና የአካባቢ አደረጃጀቶች የስርጭቱን እቅድ ለመተግበር ወሳኝ ሚና የሚጫወቱ ቢሆንም፣ ማን በየትኛው የቅድሚያ ቡድኖች ውስጥ እንደሚሆን መቆጣጠር አይችሉም።

ተጨማሪ መረጃዎች

የኮቪድ-19 ክትባት ምን ያህል ወጪ አለው?

ለ ኮቪድ-19 ክትባት ምንም ወጪ የለውም። ሜዲኬር፣ ሜዲኬይድ፣ እና ባብዛኛው የግል መድህን ዋስትና የክትባቱን ወጪ ይሸፍናሉ። ሞንትጎመሪ ካውንቲ መድህን ዋስትና ለሌለው ማንኛውም ሰው ወጪውን ይሸፍናል።

ካውንቲው የክትባቱን ፍትሓዊ ስርጭት ለማረጋገጥ በአሁኑ ወቅት የክትባት ክሊኒኮችን እያቀደ ነው።

በካውንቲው እና በሌሎች አጋሮች የሚቀርበውን የክትባት አማራጮች ላይ ያለውን ተጨማሪ መረጃ ወደ ሚቀጥለው የስርጭት ደረጃዎች ስንገባ በስፋት የምናካፍለው ይሆናል።

ከክትባቱ ኮቪድ-19 ሊይዘኝ ይችላልን?

የ ኮቪድ-19 ክትባቶች እርስዎን ለኮቪድ-19 በሽታዎች ሊያጋልጡዎ አይችሉም። በአሁኑ ወቅት ከምግብ እና መድሃኒት አስተዳደር (ኤፍዲኤ) ፍቃድ እየጠበቁ ያሉ ክትባቶች የኤምአርኤንኤ ክትባቶች ሲሆኑ፣ የ ኮቪድ-19 የሚያመጣውን ቫይረስ አይጠቀሙም።

የ ኮቪድ-19 ኤምአርኤንኤ ክትባቶች ለህዋሳቶቻችን የሚሰጡት መመሪያ “ስፓይክ ፕሮቲን” የተባለ ጉዳት የሌለው ቁራጭን እንዲያመርት ነው። ስፓይክ ፕሮቲን የሚገኘው ኮቪድ-19ን በሚያመጣው ቫይረስ የላይ ቅርፊት ላይ ነው። የመከላከያ ሲስተማችን ይህ ፕሮቲን በስፍራው መሆን እንደሌለበት በመገንዘብ የመከላከያ ምላሽ መፍጠር በመጀመር አንቲቦዲዎችን ይፈጥራል፤ ይህም ልክ በ ኮቪድ-19 የተፈጥሮ መጠቃት እንዳለው ወቅት የሚፈጠር ነው።

የኮቪድ-19 ደህንነቱ የተጠበቀ እንደሆነ እንዴት እናውቃለን?

የ ኮቪድ-19 ክትባቶች በዩናይትድ ስቴተስ ውስጥ እንዳሉ ሁሉም ሌሎች ክትባቶች ላለ ጥብቅ የደህንነት እና የውጤታማነት ደረጃዎች ያሙዋሉ ናቸው። በወረርሽኙ የተነሳ፣ የክትባቱ ምርመራዎች እና ምርቶች በተመሳሳይ ወቅት ቢደረጉም፣ የትኞቹም የደህንነት ደረጃዎች አልተዘለሉም።

ክትባቶች የሚፈቀዱት በኤፍዲኤ የተደነገጉ ጥልቅ የምርመራ እና የውጤታማነት ደረጃዎችን ካሙዋሉ ብቻ ነው። በዩናይትድ ስቴትስ ኤፍዲኤ ጥቅም ላይ የሚያውላቸው (በፈቃድ ወይም በድንገተኛ የመጠቀም ፈቃድ) የኮቪድ-19 ክትባቶች እነዚህን ደረጃዎች የሚያሟሉትን ብቻ ነው።

ተጨማሪ መረጃዎች

ክትባቱ ወረርሽኙን ያቆማል?

የ ኮቪድ-19 ን ደህንነቱ በጠበቀ እና ውጤታማ በሆነ መልኩ የሚከላከል ክትባት የመፈጠሩ ዜና ወረርሽኙን ለመዋጋት ትልቅ ግኝት ነው። ሆኖም፣ ክትባቱ ብቻውን ወረርሽኙን ወዲያውኑ አያስቆምም።

የክትባቱ መመረት እና መሰራጨት ጊዜ የሚወስድ በመሆኑ፣ ከ ኮቪድ-19 ጋር እስከ 2021 መሃል ድረስ መኖራችንን እንቀጥላለን።

ምክኒያታዊ የጥንቃቄ ድርጊቶች እንደ ጭምብል መልበስ፣ አካላዊ መራራቅ፣ አዘውትሮ እጅ መታጠብ፣ እና ትልቅ መሰባሰቦችን አለማድረግ የክትባቱ በስፋት መገኘቱን እየጠበቅን ሳለ የሚያስፈልጉ ድርጊቶች ናቸው።

ስለ ሜሪላንድ ኮቪድ-19 ክትባት እቅድ የት የበለጠ መማር እችላለሁ?

ስለ ሜሪላንድ ኮቪድ-19 ክትባት እቅድ ያሉ ጥያቄዎች ዝርዝር መልሶችን ለማግኘት, የ ኮቪድ ሊንክ ድረገጽ አዘውትረው የሚጠየቁ ጥያቄዎች ክፍልን ይመልከቱ.

መረጃዎች