የኮቪድ-19 ክትባት

ይህ ይዘት በጥር 17፣ 2022 ተረጋግጧል

 

ከዓርብ ኖቬምበር 19፣ 2021 ጀምሮ ዕድሜያቸው 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆናቸው የማጠናከርያ ክትባት ማግኘት ይችላሉ።

ክሊኒክ ይፈልጉ

የሜሪላንድ የክትባት መስጫ ቦታን ጠቋሚ ይጠቀሙ
በካውንቲ የሚተዳደሩ ክሊኒኮችን ይመልከቱ፤ ቀጠሮዎችን ይያዙ

በካውንቲው የሚተዳደር ክሊኒክ ጋር ወይም በቤት ውስጥ ቀጠሮ ለመያዝ እርዳታ ከፈለጉ በ 240-777-2982 ይደውሉ ወይም ይህን የኢሜል አድራሻ ይጠቀሙ፤ c19vaccination@montgomerycountymd.gov ። ዕድሜዎ 12 እና ከዚያ በላይ ከሆነ ወደ ካውንቲ የሚተዳደሩ ክሊኒኮች ያለቀጠሮ መምጣት ይችላሉ። ከ 5 እስከ 11 ዓመት የሆኑ ልጆች ቀጠሮ ሊኖራቸው ይገባል።

በ VA Healthcare ውስጥ ለተመዘገቡ የቀድሞ ወታደሮች ዋሽንግተን ዲሲ ቪኤ የሕክምና ማዕከል| ማርቲንስበርግ ቪኤ የሕክምና ማዕከል

ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች ወደ ቀጠሮዎቻቸው ሲመጡ፤ ይህ መመሪያ ተግባራዊ ይሆናል
ከወላጆቻቸው/አሳዳጊዎቻቸው ጋር የሚመጡ
  • ከመምጣትዎ ወይም ያለ ቀጠሮ ከመግባትዎ በፊት ቀጠሮ ይያዙ
  • ምንም ተጨማሪ ስምምነት ወይም ሰነዶች አያስፈልጉም ወላጆች/አሳዳጊዎች አስፈላጊውን መረጃ በአካል ያቀርባሉ
ዕድሜያቸው ከ12 እስከ 17 የሆነ እና ያለ ወላጅ/አሳዳጊ የሚመጡ

የክትባት መረጃዎን ቅጂ ያግኙ

ኦንላይን

የኮቪድ-19 ክትባት መረጃዎትን በሜሪላንድ MyIR ይመልከቱ። MyIR የሜሪላንድ የክትባት መረጃ አያያዝ ስርዓት ነው። እንደ የእርስዎ ይፋዊ የክትባት መረጃ ይቆጠራል።

መረጃዎትን ኦንላይን ላይ ለማግኘት ካቃትዎ የMyIR እገዛን ይጠቀሙ። የእርስዎ መረጃ በMyIR ላይ ካልታየ፣ ለ"ያልተዛመደ መረጃ "እገዛ ይጠይቁ።

ቅጂ ኢሜል ያድርጉ

በካውንቲ የሚተዳደር ክሊኒክ የተከተቡ ከሆነ፣ የእርስዎን መረጃ ቅጂ በኢሜል ልንልክልዎ እንችላለን። ቅጂ ለመጠየቅ በዚህ ኢሜይል ይጠቀሙ c19vaccination@montgomerycountymd.gov ወይም 240-777-2982 ይደውሉ።

ተጨማሪ የሲዲሲ የክትባት ካርዶችን ማቅረብ አንችልም።

የሁለተኛ ክትባት ቀጠሮዎች

ለሁለተኛ ክትባት መመዝገብ አያስፈልግም! ቀጠሮ እንዲይዙ መልክት እንልክልዎታለን።

በ ሁለተኛ ክትባት ዙሪያ ስለምንልክልዎ ኢሜይሎች የበለጠ ይወቁ

የክትባት ጣቢያ መረጃ

የክሊኒክ ቦታ ማሳያ ካርታዎችን፣ የአውቶብስ አገልግሎት አማራጮችን እና ለአሽከርካሪዎች አቅጣጫ ጠቋሚ መረጃዎችን ይመልከቱ፤

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የክትባት ስርጭት ዳሽቦርድ

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የክትባት ስርጭት ዳሽቦርድ ይመልከቱ